ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ቼልሲ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ቼልሲ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ !
ቼልሲ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሌክስ ስኮትን ለማስፈረም ያቀረበው የዝውውር ጥያቄ በበርንማውዝ ውድቅ ሆኗል።

ቼልሲ አቅርቦ የነበረው የዝውውር ሂሳብ 6️⃣4️⃣ ሚልዮን ፓውንድ እንደሚጠጋ ተዘግቧል።

በርንማውዝ እስከ 2028 ውል ያለው አሌክስ ስኮት በክለቡ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

የ 22ዓመቱ አማካይ አሌክስ ስኮት በተጨማሪም በማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል እየተፈለገ ይገኛል።

ቀያዮቹ ሰይጣኖች ሁለት አማካዮች ቢያስፈርሙም ሶስተኛ የማምጣት እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል።

አርሰናል እና ቼልሲ የተጫዋቹን ሁኔታ አሁንም መከታተላቸውን እንደቀጠሉ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች