ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ታዘጋጃለች !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ታዘጋጃለች !
ኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ታዘጋጃለች !

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከወራት በኋላ የመስማት የተሳናቸው የእግር ኳስ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ታዘጋጃለች።

ኢትዮጵያ ውድድሩን ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግድ ሲሆን ከ 18 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአሁኑ ሰዓት የአፍሪካ መስማት የተሳናቸው እግርኳስ ኮንፌደሬሽን ሀላፊዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ይገኛሉ።

ሀላፊዎቹ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በቆይታቸውም በውድድሩ ዝግጅት ዙሪያ መወያየታቸውን አሳውቀዋል።

ልዑክ ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ መስማት የተሳናቸው እግርኳስን ለማሳደግ ላደረገው ድጋፍ አመስግኗል።

ውድድሩ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከግምገማው በኋላ ሀላፊዎቹ የካፍን መስፈርት ያሟሉ መሰረተ ልማቶችን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ከኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው አሶሴሽን ጋር በመተባበር ውድድሩ ይደረጋል።

ውድድሩ ከኅዳር 21 እስከ ታኅሣሥ 4/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች