ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የሊቨርፑል እና ኖቲንግሀም ጨዋታ ምን አስመለከተን ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የሊቨርፑል እና ኖቲንግሀም ጨዋታ ምን አስመለከተን ?
የሊቨርፑል እና ኖቲንግሀም ጨዋታ ምን አስመለከተን ?

አዲሱ የመርሲሳይዱ ክለብ አሰልጣኝ አዶኒ ኢራኦላ ተከታታይ ጨዋታቸውን ሁለት አቻ በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

አዲሱ የቡድኑ አሰልጣኝ የጠበቁትን ውጤት ባያገኙም በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ይታመናል።

የፎረስት አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር በበኩላቸው በአጭር ጊዜ በክለቡ ያሳዩት ምርጡ መርሐ ግብር እንደሆነ ይታመናል።

ኦሊቨር ግላስነር ከሜዳቸው ውጪ ወደ አንፊልድ ተጉዘው የመጀመሪያ ነጥባቸውን በአዲስ የውድድር አመት ማሳካት ችለዋል።

በጨዋታው ሁለቴ መምራት የቻሉት ኖቲንግሀም ፎረስቶች ወሳኝ ነጥብ ከሜዳቸው ውጪ ይዘው ወጥተዋል።

ሊቨርፑል የባርኮላን ዝውውር በማጠናቀቅ የፊት መስመሩን እያጠናከረ ይገኛል።

ነገር ግን  ቡድኑ ባለፉት ጨዋታዎች ላይ ያሳየው ክፍተት በሌሎች የሜዳው ክፍሎች ላይ አዲስ ተጫዋች እንዲያስፈርም ፍንጭ የሰጠ ሆኗል።

ሊቨርፑል ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በሊጉ አራት ጎሎች ሊቆጠርባቸው ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች