ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ፒኤስጂ የባርኮላን መሸጫ ዋጋ አሳወቀ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ፒኤስጂ የባርኮላን መሸጫ ዋጋ አሳወቀ !
ፒኤስጂ የባርኮላን መሸጫ ዋጋ አሳወቀ !

ፒኤስጂ በሊቨርፑል እየተፈለገ የሚገኘው ብራድሌይ ባርኮላ መሸጫ ዋጋ 1️⃣7️⃣0️⃣ሚልዮን ዩሮ መሆኑን አሳውቋል።

የ 23ዓመቱ ተጨዋች ባርኮላ በፒኤስጂ ያለው ኮንትራት በ 2028 ሲጠናቀቅ ውሉን የማራዘም ፍላጎት የለውም።

ፒኤስጂ ይህንን ዋጋ እንዲያወጣ ያሳሰበው ቼልሲ ለሞርጋን ሮጀርስ እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ ለአንደርሰን የከፈሉት ገንዘብ መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም ወጣት መሆኑ ፤ ለፈረንሳይ ቋሚ መሆኑ እና በክለቡ ተከታታይ የሻምፒየንስ ሊግ ስኬት ውስጥ ያበረከተው አስተዋጽኦ ዋጋውን ከፍ አድርጎታል ተብሏል።

ከሊቨርፑል በተጨማሪም ሌላ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ወደ ፉክክሩ ሊገባ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በቡድናቸው የሚፈልጉት ቁርጠኛ ተጨዋቾችን ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት ለክለቡ ጥሩ ዋጋ ካልቀረበለት እና ካልተሸጠ ባርኮላ ቀጣይ አመት በፒኤስጂ እንደማይጫወት ተዘግቧል።

መረጃው የ ዘ አትሌቲክ ነው።

ተዛማጅ ታሪኮች