" በተኩሱ የተጠቁት ተሽከርካሪዎች ህጻናት ያሏቸው ወላጆችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን ያሳፈሩ ነበሩ " - ነዋሪ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" በተኩሱ የተጠቁት ተሽከርካሪዎች ህጻናት ያሏቸው ወላጆችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን ያሳፈሩ ነበሩ " - ነዋሪ
በጋምቤላ ክልል አቦል ወረዳ፣ ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን በእጀባ ሲጓዙ በነበሩ የህዝብ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ተኩስ 16 ሰዎች መገደላቸውንና 57 ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
ጥቃቱ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ በአቦል ወረዳ አካባቢ መፈጸሙን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። በጥቃቱ የተሳተፉት ታጣቂዎች በህዝብ የተሞሉ ስድስት ተሽከርካሪዎች ላይ ተኩስ እንደከፈቱም ተናግረዋል።
አንድ ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ በሰጡት መረጃ፣ " በታጣቂዎች የተገደሉት 16 ሰዎች ናቸው፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ 57 ሰዎች ናቸው " ብለዋል።
ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው፣ 12 ሰዎች በጥቃቱ ቦታ ላይ ሲሞቱ፣ ሌሎች 4 ሰዎች ደግሞ በኋላ በሆስፒታል ሕክምና ላይ እያሉ ሕይወታቸውን እንዳጡ ገልጸዋል። በእርሳቸው መረጃ የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር 53 ነው።
በሟቾችና በቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ላይ የተለያየ መረጃ መኖሩን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሌሎች ነዋሪዎችም ማብራሪያ ጠይቋል።
ሌላኛው ነዋሪ በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር 16 ፣ የቆሰሉት 57 መሆናቸውን ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፣ ተሽከርካሪዎቹ ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን የሚጓዙ መደበኛ የህዝብ አውቶቡሶች ሲሆኑ፣ በእጀባ ከጋምቤላ ከተማ ተነስተው ነበር። ከተሽከርካሪዎቹ ጋር የመንግስት የጸጥታ አካላትም አብረው ይጓዙ እንደነበር ገልጸዋል።
ከነዋሪዎቹ አንዱ፥ ተሽከርካሪዎቹ ከጋምቤላ ከተማ ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ እንደተነሱ ገልጸው፣ "አካዴ" የሚባል አካባቢ ሲደርሱ ጥቃቱ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል። እንደ ነዋሪው ገለጻ፣ "አካዴ" ከአቦል ወረዳ በመኪና የ10 ደቂቃ ያህል ርቀት ላይ ይገኛል።
በአካባቢው ያለው መንገድ በከፊል የተበላሸ በመሆኑ ተሽከርካሪዎች በፍጥነት መጓዝ እንደማይችሉ ነዋሪው ገልጸዋል። በዚያ አካባቢ ታጣቂዎች እንደሚገኙም ገልጸው፣ ተሽከርካሪዎቹ በእጀባ እየተጓዙ ሳሉ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ተናግረዋል።
" ታጣቂዎቹ በትላልቅ መሳሪያዎች ተኩስ ከፍተዋል፤ ተኩሱም ህዝብ ባሳፈሩ ስድስት ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተከፈተው " ሲሉ ነዋሪው ገልጸዋል።
በአካባቢው ከ10 በላይ ተሽከርካሪዎች እየተጓዙ እንደነበር፣ ነገር ግን ተኩሱ ያነጣጠረው በስድስት መኪናዎች ላይ መሆኑን ደግመው ተናግረዋል።
እንደ ነዋሪው ገለጻ፥ በተኩሱ የተጠቁት ተሽከርካሪዎች ህጻናት ያሏቸው ወላጆችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን ያሳፈሩ ነበሩ። በዚህ የመንገድ ክፍል ቀደም ሲልም ተመሳሳይ ጥቃቶች መከሰታቸውን ገልጸው በቅርቡ ግን ሁኔታው እየከፋ መምጣቱን ተናግረዋል።
በጥቃቱ ምክንያት በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥቃቱን በተመለከተ የጋምቤላ ክልል ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ሞክሯል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ግን "ወደ ጸጥታ ቢሮ ደውሉ " ብለው ምላሽ ሰጥተዋል። የጸጥታ ቢሮው ስልክ እየተነሳ እንዳልሆነ ለፕሬዚዳንቷ ሲገለጽላቸውም፣ " እነርሱ ጋር ደውሉ፤ ሥራ ላይ ሆነው ይሆናል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማብሄር ኮር ከቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ተደርጎላቸው አልመለሱ። ለተላከላቸው የጽሑፍ መልዕክትም ወዲያው ምላሽ አልሰጡም።
የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦጁሉ ጊሎ በበኩላቸው፣ " ገና አላጣራንም፤ እነርሱ ራሳቸው (የጸጥታ ክፍሉ) ናቸው መረጃ የሚያቀብሉን። እነርሱ ሲሰጡኝ ነው መረጃ የምሰጠው " ብለዋል።
ይሁን እንጂ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጉዳት መድረሱን ለዶቼቬለ አረጋግጧል። ከዚህ ውጭ ግን በሟቾችና በቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ላይ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጠም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአቦል ወረዳ አመራሮችን ለማነጋገር ያደረገው ጥረትም አልተሳካም።
በተጨማሪም የጋምቤላ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስተን ስለጥቃቱ ለተጠየቁት ጥያቄ፣ " አሁን ሌላ ሥራ ላይ ስለሆንኩ ምላሽ መስጠት አልችልም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia