" በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው ዝናቡ የወረደውና ከባድ አደጋ ያደረሰው " - አቶ ጋቾ አምቦ የሀዋሳ ከተማ አደጋ ስጋት ኃላፊ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው ዝናቡ የወረደውና ከባድ አደጋ ያደረሰው " - አቶ ጋቾ አምቦ የሀዋሳ ከተማ አደጋ ስጋት ኃላፊ
በሀዋሳ ከተማና አከባቢዋ ትናንት ከሠዓት በኋላ በረዶና ነፋስ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ የአደጋ ስጋት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጋቾ አምቦ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው ዝናቡ የወረደውና ከባድ አደጋ ያደረሰው " ያሉት አቶ ጋቾ በሀዋሳ ከተማ በተለይም ቱላ ፣ መናኻሪ፣ መሃል፣ ባህል አደራሽ፣ ምስራቅና ታቦር ክፍለ ከተሞች ዝናቡ ሰፋ ያለ ጉዳት መከሰቱን አስረድተዋል።
" በቱላ ክፍለ ከተማ የአንዲት እናት ሕይወት አልፏል " ያሉት ስራ አመራር ኃላፊው 11 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶ ወደ ሕክምና ተቋም መወሰዳቸውንም ገልፀዋል።
ከተጎጂዎች መካከል በአንድ ቤት ውስጥ የነበሩ የቤተሰብ አባላትና በአንድ የመብራት ምስሶ ስር የነበረ አንድ ወጣት ይገኝበታል።
ቁጥርራቸው በውል ያልተለዩ መኖሪያ ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና የዛፎችና የኤሌክትሪክ ምሶሶዎች በመወዳደቃቸው ሌሊቱን መብራት ተቋርጦ ማደሩን አስታውቀዋል።
በአደጋው የተጎዱ ነዋሪዎችን ለመደገፍ ግብረሃይል መቋቋሙንና ጉዳት የደረሰባቸውን የማሳከም፤የቤት እና የመብራት አገልግሎት ጥገና እየተከናወነ ስለመህኑም አቶ ጋቾ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
ሃምሌ 23 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia