ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ሥራ ፈላጊዎች በእስያ የማጭበርበሪያ ካምፖች ተጠቂ እየሆኑ ነው።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ሥራ ፈላጊዎች በእስያ የማጭበርበሪያ ካምፖች ተጠቂ እየሆኑ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (አይኦኤም) ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያንን ጨምሮ ከምሥራቅ አፍሪካ የሚሄዱ ሥራ ፈላጊዎች በደቡብ ምሥራቅ እስያ በሚገኙ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ካምፖች ተጠቂ የመሆን አደጋ በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን አስጠንቅቋል።
ኤጀንሲው እንደገለጸው፣ የወንጀል መረቦች በውጭ አገር ከፍተኛ ደመወዝ የሚያስገኙ ሥራዎች እንዳሉ በማታለል ሥራ ፈላጊዎችን ይመለምላሉ። ተጎጂዎቹ መድረሻቸው ሲደርሱ ፓስፖርታቸው ይወሰድባቸዋል፤ በጥብቅ ጥበቃ ስር በሚገኙ ካምፖች ውስጥ በማስፈራራት፣ በድብደባና በሌሎች ስቃዮች የኦንላይን ማጭበርበር እንዲፈጽሙ ይገደዳሉ።
አይኦኤም ከ2022 እስከ 2025 ባለው ጊዜ በደቡብ ምሥራቅ እስያ ለግዳጅ ወንጀል ከተወሰዱ 39 አገራት የመጡ ከ3,500 በላይ ተጎጂዎችን መደገፉን ገልጿል። ከእነዚህም መካከል ከኢትዮጵያና ከኬንያ የመጡ ሰዎች እንዳሉ ቢገልጽም፣ ትክክለኛ ቁጥራቸውን አላሳወቀም።
ኤጀንሲው እንደሚለው፣ ከካምፖቹ የተረፉ ሰዎች በማጭበርበር ሥራ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ድብደባ፣ ፆታዊ ጥቃት፣ ረሃብ እና ብቻቸውን መታሰር እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
የአይኦኤም የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ፍራንትዝ ሴሌስቲን፣ "ምሥራቅ አፍሪካውያን በማጭበርበሪያ ካምፖች መገኘታቸው የሰዎች ዝውውር ከእንግዲህ የሩቅ ስጋት እንዳልሆነ ያሳያል" ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የወንጀልና የአደንዛዥ ዕፅ ቢሮ (UNODC) እንደሚያመለክተው፣ በምያንማር፣ ካምቦዲያና ላኦስ የተስፋፉት እነዚህ የማጭበርበሪያ ካምፖች በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ገቢ ያስገኛሉ።
በምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ እስያ ብቻ የሚፈጸሙ የኦንላይን ማጭበርበሮች ባለፈው ዓመት ከ88 እስከ 114 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዳስገኙም ተገልጿል።
አይኦኤም መንግሥታት በእነዚህ ካምፖች ውስጥ በግዳጅ የተሰማሩ ሰዎችን እንደ ወንጀለኛ ሳይሆን እንደ የሰዎች ዝውውር ተጎጂዎች እንዲመለከቷቸው ጥሪ አቅርቧል።
በተጨማሪም ሥራ ፈላጊዎች ከውጭ የሚቀርቡላቸውን የሥራ ዕድሎች በጥንቃቄ እንዲያጣሩ፣ ያልተለመደ ከፍተኛ ደመወዝ፣ ፈጣን የሥራ ቅጥር ወይም ከእውነታ የራቁ የሥራ ቃል ኪዳኖች ሲቀርቡላቸው እጅግ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ሃምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia