የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለት የሚዲያ ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለት የሚዲያ ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ባለሥልጣን መ/ቤቱ፤ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ለአሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 እና አርትስ ቴሌቪዥን ነው።
" የሚዲያ ተቋማቱ የተሰጣቸውን የይዘት ግዴታዎች በመተላለፍ ለተከታታይ ጊዜ ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ መረጃ በማሰራጨታቸው የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል " ሲል ነው ያሳወቀው።
" ከሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በተደጋጋሚ በታዩ የሕግና የሙያ ጥሰቶች ላይ ውይይት ባድረግም ጉልህ ለውጥ ባለመታየቱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያው ተሰጥቷል " ብሏል።
" ሁለቱ የሚዲያ ተቋማት በቀጣይ ሥራቸውን በሕግና በሙያ ሥነ ምግባር መሠረት እንዲያከናውኑ " ያሳሰበው ባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ተመሳሳይ ጥሰቶች ከቀጠሉ በሕጉ መሠረት ተጨማሪ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
" ሁሉም የሚዲያ ተቋማት በዘገባ ሥራቸው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን፣ የሀገሪቱን ሕጎችና የሙያ ሥነ ምግባርን አክብረው መስራት ግዴታቸው ነው " ሲልም አሳስቧል።
ሃምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia