የመሬት እና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ አረጋግጫለሁ ሲል የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አሳውቋል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የመሬት እና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ አረጋግጫለሁ ሲል የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አሳውቋል።
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው የሙስና ግንዛቤ ዳሰሳ ጥናት፦
- በመሬት አስተዳደርና ይዞታ ምዝገባ፣
- በገቢዎችና ታክስ፣
- በኮንስትራክሽን ፈቃድና ቁጥጥር፣
- በንግድና ትራንስፖርት፣
- በወረዳና ቀበሌ አስተዳደሮች ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ለዳሰሳ ጥናት በተወሰደ ናሙና ከ6ዐ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስና በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተግባራት ከፍተኛ እንቅፋትና ችግር የፈጠረ አሳሳቢ ችግር መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡
በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት፣ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ውስብስብና ግልጽ ያልሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደቶችና የሕግ ማስከበር ድክመቶች ለሙስና መስፋፋት ዋነኛውንና ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ የጥናት ሪፖርት ያመለክታል፡፡
በጥናቱ ጉቦ ለመስጠት የሚገደዱ ሰዎች ለድርጊታቸው የሚያቀርቡት አንዱ ምክንያት አገልግሎቱን ለማግኘት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ግለሰቦች ጉቦ የሚሰጡት የሚፈልጉት አገልግሎት እንዲፈጸምላቸውና የሚጠበቅባቸውን ባለማድረጋቸው ሊደርስባቸው የሚችለውን እንግልት ለማስቀረት እንዲሁም ጉዳያቸው በፍጥነት እንዲፈጸምላቸው መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡
የሙስና ድርጊትን ለመጠቆም የሚፈልጉ ግለሰቦች ሊደርስባቸው የሚችል የበቀል ዕርምጃና የማስፈራራት ሥጋት በመኖሩ፣ አስተማማኝ የጠቋሚዎች ጥበቃ ሥርዓት ማነስ፣ እንዲሁም የጥቆማ አሰጣጥ ሒደቱ ረዥምና ውስብስብ መሆን ኅብረተሰቡ ሙስና ለመጠቆም ሥጋት እንዳለበት በጥናቱ ተገልጿል።
ከጥናቱ ተሳታፊዎቹ 75 በመቶ የሚሆኑት በሙስና ጥፋተኞች ላይ ፈጣንና ጠንካራ የሕግ ቅጣት መውሰድ እና የተመዘበረ ሀብትን ማስመለስ ሙስናን ለመቀነስ ውጤታማ እርምጃዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ የሙስና ወንጀል ሕግ ማስከበር ሂደትን በተመለከተም ተጨማሪ የአሠራር ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
በተለይም በተቋማት መካከል የመረጃ ልውውጥና የውሳኔ አፈጻጸም መዘግየት፣ የማስረጃ አሰባሰብ ውስንነት፣ የዲጂታልና ፎረንሲክ ምርመራ አቅም ማነስ እና የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት በሙስና ምርመራና ክስ ሂደት ላይ እንቅፋት መሆናቸውን አመልክቷል።
ኮሚሽኑ የሕግ ማስከበር ሂደቱ ግልጽ፣ ተጠያቂነት ያለው፣ ተገማችና ውጤታማ እንዲሆን ቀጣይነት ያለው የአሠራር ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ጠቁሟል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia