ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች ተያዥ ያለው ጥበቃ ቅጠሩ ክትትልም አድርጉ " - ፖሊስ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች ተያዥ ያለው ጥበቃ ቅጠሩ ክትትልም አድርጉ " - ፖሊስ
" የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች ተያዥ ያለው ጥበቃ ቅጠሩ ክትትልም አድርጉ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ መስከረም 19/2019 ዓ/ም ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት በለሚ ኩራ ክ/ ከተማ ወረዳ 9 ሰሚት ኮንዶሚኒየም 2ኛ በር አካባቢ 2 ሲኖትራክ ተሽከርካሪዎችን ከማቆሚያቸው ሰርቀው የተሰወሩ 3 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

የግል ተበዳዮች እና የተሽከርካሪ ማቆሚያው ጥበቃ ኃላፊ በሰዓቱ ወደ ጎሮ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በአካል ቀርበው ጥቆማ በመስጠታቸው ፖሊስ ወዲያውኑ ወደ ስፍራው በመሄድ ወንጀሉ መፈጸሙን አረጋግጧል።

በዚህም የሰሌዳ ቁጥሩ " ኮድ 3 59732 ኢት " ከቆመበት ቦታ አንስተው በአካባቢው በመሸሸግ ሌላ "ኮድ 3_53262 ኢት" የሆነ ተሽከርካሪን ደግሞ ይዘው በመሰረው ፦
- ኢብራሂም የኑስ፣
- ነጅመድን ሬድዋን እና ኑረዲን በርጌቾ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ክትትል ተደርጎባቸው በሸገር ከተማ አንፎ አደባባይ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ወቅት ፦
- ለወንጀል ድርጊት መሣሪያነት ሲጠቀሙበት የነበረ ባለቤትነቱ ለጊዜው ያልታወቀ የሰሌዳ ቁጥር "ኮድ 2 C15420 አ/አ" የሆነ ራቭ ተሽከርካሪ፣
- የሰሌዳ ቁጥር "ኮድ 3 A10747 ኢት" (የፊትና የኋላ) እና የሰሌዳ ቁጥር "ኮድ 3 65681 ኢት" ሰሌዳዎች፣
- ለወንጀል ማከናወኛ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ የተሽከርካሪ ቁልፎች ... ተይዘዋል።

ፖሊስ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ላይ ተደራጅተው የሚሰሩ አካላት ሕጋዊ መንገድን የተከተለ ተያዥ ያለው ጥበቃ ከመቅጠር ባለፈ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስቦ፤ ባለቤቶችም ተሽከርካሪዎቻቸው ላይ ጂፒኤስ (GPS) በማስገጠም የበኩላቸውን ቁጥጥር እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል።

መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች