የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮች አበበ አካሉና ይሳቅ ወልዳይ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉስ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮች አበበ አካሉና ይሳቅ ወልዳይ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉስ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው እና የኢሕአፓ አመራሮች ለቢቢሲ አማርኛ ገልጸዋል።
በቅድሚያ የተያዙት ጠበቃ የሆኑት አበራ ንጉስ ሲሆኑ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በማለዳ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ "ለምርመራ እንደሚፈለጉ" በመግለጽ ይዘዋቸዋል። ነገር ግን የተያዙበት ምክንያት በዝርዝር እንዳልተገለጸ ተነግሯል።
በዚያው ቀን የኢሕአፓ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ይሳቅ ወልዳይም በመኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አብርሃም ሃይማኖት ገልጸዋል።
ከዚያም የኢሕአፓ አመራር አቶ አበበ አካሉ ከመኖሪያ ቤታቸው ውጭ በነበሩበት ስፍራ መያዛቸው ተነግሯል።
የፓርቲው ኃላፊዎች እንደሚሉት፣ ሦስቱም ግለሰቦች ወደ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ሜክሲኮ) መወሰዳቸው ታውቋል። ሆኖም እስከ ዜናው ዝግጅት ድረስ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳልተገናኙና ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ተገልጿል።
የፌደራል ፖሊስ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አሁን ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia