የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለ52 የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ መስጠቱን ገለጸ። በዚህም በሕጋዊ ፈቃድ የሚሰሩ ሚዲያዎች ቁጥር 329 ደርሷል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለ52 የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ መስጠቱን ገለጸ። በዚህም በሕጋዊ ፈቃድ የሚሰሩ ሚዲያዎች ቁጥር 329 ደርሷል።
ባለሥልጣኑ በ2019 በጀት ዓመትም የሚዲያ ዘርፉን ለማጠናከር የክትትል፣ የድጋፍና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እንደሚያጠናክር ገልጿል።
በ2018 በጀት ዓመት በተጨማሪ ለ14 የበየነ መረብ ሚዲያዎች፣ ለ5 የማህበረሰብ ብሮድካስት ሚዲያዎች ፈቃድ ሲሰጥ፣ ለ19 የሚዲያ ፕሮግራም አዘጋጆች፣ ለ9 የማስታወቂያ አዘጋጆች፣ ለ5 ቋሚ የውጭ ዜና ወኪሎች እና ለ78 የውጭ ጋዜጠኞችና ዘጋቢዎች ፈቃድ መሰጠቱ ተገልጿል።
ባለሥልጣኑ የሚዲያ ምህዳሩን የበለጠ ለማሳደግና የሚዲያዎች ለሀገር ሰላም፣ ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም የሚያበረክቱትን ሚና ለማጠናከር ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia