የኢትዮጵያ አየር መንገድ 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ።
🛫 በበጀት አመቱ 20.7 ሚሊየን ደንበኞች አጓጉዟል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ 2025/2026 በጀት አመት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ዛሬ አቅርቧል።
ሪፖርቱ ያቀረቡት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ናቸው።
አቶ መስፍን በጀት አመቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብዙ የሰራበት እና የተንቀሳቀሰበት ጥሩ አመት ነበር ብለዋል።
በተለይም የመጀመሪያዎቹ ሩብ አመታት አመቺ የስራ ጊዜ ነበሩ ያሉ ሲሆን በበጀት አመቱ ማጠናቀቂያ አካባቢ በገልፍ ሃገራት የተፈጠረው ችግር የተወሰነ ተጽዕኖ ቢያመጣም በአጠቃላይ ጥሩ አመት ነበር በማለት አክለዋል።
በበጀት አመቱ 4 አዳዲስ አለም አቀፍ መዳረሻዎችን በመጨመር አለም አቀፍ የመዳረሻዎችን ቁጥር ወደ 150 ከፍ ማድረጉን ፣የሃገር ውስጥ ማዳረሻዎችንም ብዛት ከ 22 ወደ 25 ከፍ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።
9 አዳዲስ አውሮፕላኖች በግዢ እና በኪራይ በበጀት አመቱ ወደ ስራ መግባታቸውንም አስታውሰዋል።
በአመቱ የተደረጉ በረራዎች በሰዓት ሲታይ ቀደም ሲል ከነበረው በጀት አመት 8 በመቶ እድገት እንዳለው ይህም ከእቅዱ 96 በመቶ መሆኑን እንዲሁም 20.7 ሚሊየን ደንበኞች መጓጓዛቸውና ይህም ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር 10 በመቶ እድገት ቢኖረውም ከእቅዱ አንጻር 98 በመቶ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አየር መንገዱ ያጓጓዘው ጭነትም ከባለፈው በጀት አመት የ 16 በመቶ እድገት አለው ብለዋል።
በአጠቃላይ የተደረገው በረራ እና የተጓጓዘው ጭነት ካለፈው በጀት አመት ከ 8 እስከ 16 በመቶ ጭማሪ ቢያሳይም ከእቅዳችን ግን በተወሰነ መጠን ቅናሽ ያሳያል ነው ያሉት።
ይህ የሆነበትን ምክንያት ሲያብራሩም "በገልፍ ሃገራት ባጋጠመው ጦርነት አየር መንገዱ ወደ ቀጠናው ያደርጋቸው የነበሩ 10 የሚሆኑ በረራዎችን የተቋረጡ በመሆኑ ፣የትላልቅ የአውሮፕላኖች እጥረት ፣አሜሪካ አዳዲስ የጉዞ ማዕቀቦች በመጣሏ ምክንያት በአፍሪካ እና በሰሜን አሜሪካ መካከል ጉዞ በመቀነሱ ወደ ኮንጎ እና ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሃገራት ዜጎች እንዳይጓዙ ሃገራት ክልከላ በማድረጋቸው የ እቅዳችንን ሙሉ በሙሉ እንዳናሳካ ሆነናል"ብለዋል።
አየር መንገዱ በበጀት አመቱ 9.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አቶ መስፍን ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ የአየር መንገዱ ወጪ ከእዚህ ቀደም ከነበረበት የ 25 በመቶ ጭማሪ ያለው መሆኑን ገልጸዋል ይህም በገልፍ ሃገራት ጦርነት ሳቢያ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 22 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia