ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ፣ የሀገር ሀብት ለመዝረፍ እና ሕገ-ወጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ በተንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ተቋማት …

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ፣ የሀገር ሀብት ለመዝረፍ እና ሕገ-ወጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ በተንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ተቋማት …
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ፣ የሀገር ሀብት ለመዝረፍ እና ሕገ-ወጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ በተንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ሰፊ የሕግ ማስከበር እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል።

በመግለጫው መሠረት፣ እርምጃዎቹ በፋይናንስ፣ በንግድ፣ በነዳጅ፣ በማዕድን፣ በገቢዎችና ጉምሩክ፣ በቤቲንግና ፊንቴክ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዘርፎች ውስጥ በተፈጸሙ የሙስና፣ የኮንትሮባንድ፣ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሌሎች የኢኮኖሚ ወንጀሎች ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተገልጿል።

መግለጫው እንደሚያመለክተው፣ ከ7 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ታሽገዋል፤ 169 ግለሰቦች በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጉዳይ፣ 183 ግለሰቦች በወርቅ ኮንትሮባንድ፣ ከ650 በላይ ግለሰቦችና ተቋማት ደግሞ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ጉዳይ የሕግ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። በተጨማሪም 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ መታገዳቸው ተገልጿል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ መንግሥት ሙስናን፣ ሌብነትንና ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል የጀመረውን እርምጃ በቀጣይነት እንደሚያጠናክር ገልጸው፣ ሕብረተሰቡም ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን በማጋለጥና ከሕገ-ወጦች ጋር ባለመተባበር ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች