ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ኤርትራ አሰልፋቸዋለች  ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ኤርትራ አሰልፋቸዋለች  ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ
" የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ኤርትራ አሰልፋቸዋለች  ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣  የኤርትራ መንግሥት ከግብፅ ጋር በመሆን የምስራቅ አፍሪካን ሰላም ለማናጋት እና ቀጣናውን ለማተራመስ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ከ " Pulse of Africa " ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

በኤርትራ ያለው ከባድ የኑሮ ውድደት እና መጥፎ የፖለቲካ ሁኔታ በርካታ ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ማድረጉን ያነሱት አቶ ጌታቸው " የሀገሪቱ ሠራዊትም ሀገር ለመጠበቅ ሳይሆን ፕሬዚዳንቱን ለመጠበቅ ብቻ የቆመ ነው " ብለዋል።

በዚህም ምክንያት ኤርትራ ራሷ በቀጥታ በጦርነት ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ ሌሎች ታጣቂዎችን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ግጭቶችን ከድንበሯ ራቅ ባሉ ቦታዎች ለማቀጣጠል እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው እንዳሉት፤ እንደ ፋኖ፣ ኦነግ ሸኔ እና አሁን ደግሞ ሕወሓት ያሉ አካላት የኤርትራን ዓላማ ለማሳካት እና የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ተሰልፈዋል።

በተለይም ሕወሓት እና የኤርትራ መንግሥት አብረው መሠለፋቸው እጅግ አደገኛና የትግራይንና የአማራን ሕዝብ ለከፋ ሁኔታ የሚዳርግ መሆኑን አስረድተዋል።

" የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እስካሁን ለሚደርሱበት የተለያዩ ትነኮሶዎች ከፍተኛ ትዕግስት እያሳየ ይገኛል " ያሉት አቶ ጌታቸው  ሆኖም ሕወሓት በኤርትራ ወጥመድ ወድቆ በፌዴራል ኃይሎች ላይ ጥቃት ከሰነዘረ፣ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አጽንኦት ሰጥተው አስጠንቅቀዋል።

ቀጣናውን ከሌላ አስከፊ ጦርነት ለመታደግ እና የሰላም አፍራሾችን እንቅስቃሴ ለመግታት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኤርትራ መንግሥት እና ተባባሪዎቹ ላይ አፋጣኝ እና ጠንካራ ጫና መፍጠር እንዳለበት አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች