በካማሽ ዞን የሰዎችን ህይወት እስከመንጠቅ ተደጋጋሚ የታጣቂዎችን ጥቃት ሲያስተናግድ በቆዬ ቦታ ሰሞኑንም የከፋ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

በካማሽ ዞን የሰዎችን ህይወት እስከመንጠቅ ተደጋጋሚ የታጣቂዎችን ጥቃት ሲያስተናግድ በቆዬ ቦታ ሰሞኑንም የከፋ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ምዥጋ ወረዳ "አንገር ሜጢ" ወይም "አይሻንጅድም" በተባለ ቀበሌ ላይ የታጠቁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት፣ በሰዎች ላይ ጉዳት መደረሱን፣ በርካቶች መፈናቀላቸውን፣ በቤትና ንብረት ላይ አስከፊ ውድመት መድረሱን ነዋሪዎችና የክልሉ ምክር ቤት አባል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የካማሽ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አመራር ጥቃቱ መፈጸሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። የክልሉ ም/ቤት አባል አቶ ለሜሳ ኔኖ፣ "ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል" ብለዋል።
በፊትም "የሸኔ ታጣቂ ቡድን ተደጋጋሚ ጥቃት ፈጽሞበት በነበረው አንገር ሚጤ ቀበሌ ሰሞኑንም በርካታ ቤቶች አቃጥሎ አውድሟል። የቁም ከብቶችም ዘርፎ ነዋሪዎቹ ወደ ጫካ ተበታትነው በሕይወት መኖራቸው አስጊ ላይ ነው" ሲሉም ገልጸዋል።
በአካባቢው ከሁለት ቀናት በፊት የተኩስ ሩምታ እንደነበር ገልጸው፣ "ቤት ብቻ ሳይሆን ከቤት ውስጥ የነበረ የእህል ማከቻ ጎተራ ጭምር ነው ያወደሙት። ጥቃቱ ሲፈጸም ዘንድሮ ብቻ የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ ነው በማለት ጥቃቱ መደጋገሙን አስረድተዋል።
ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ?
አንድ ነዋሪ በሰጡን ቃል፣ ከአምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፣ ከ1 ሺሕ በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል ተብሎ እንደሚገመት ገልጸዋል። በመቶዎች ኩንታል የሚገመት እህል መቃጠሉን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች ተነድተው መወሰዳቸውንም ተናግረዋል።
ሌላኛው የዓይን እማኝ ነዋሪ፣ "አይሻንጅድም ቀበሌ ላይ ትልቅ ችግር ነው የተፈጠረው እኔም እዛው ነበርኩ። ጥቃቱ ቦታው ላይ ተደጋጋሚ ሆኗል፤ አሁን ለሦስተኛ ጊዜ ነው የተፈጸመው፤ ታጣቂዎቹ ከተማ ላይ ገቡ፤ ከዚያ በኋላ ቤት ማቃጠል ጀመሩ፤ ህዝቡም በየጫካ ነው የተበተነው" ሲሉ ነግረውናል።
ነዋሪዎቹ የት እንደደረሱ እየተፈለገ መሆኑን በማስረዳት፤ "በህይወት የት አካባቢ እንዳሉ እንኳ አይታቅም" ያሉት ነዋሪው፣ "ይህን ድርጊት የፈጸመው የተቀናጄ ኃይል ነው፤ 'ገዳ ኮማንዶ' የሚባልም አለበት፣ 'ኦነግ ሸኔ'ም አለበት" ብለዋል።
ተጎጂዎችም እንዳሉ ገልጸው፣ "የጠፉትን ለመፈለግም ተቸግረናል። የሚመለከተው አካል ይድረስልን። ቤቶችን በነዳጅ ነው ያቃጠሏቸው። የተቀመጡ ምርቶ ተቃጥለዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላኛው ነዋሪ፣ መንግስት "ሸኔ" ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በዚሁ ቀበሌ፣ ጥቃት መፈጸሙን ገልጸው፣ "ፍላጎቱ ምን እንደሆነ ባናውቅም፤ ጥቃቱ ዘንድሮ ብቻ አሁን ለሦስተኛ ጊዜ ነው የተፈጸመው። የአሁኑ ጥቃት ከበድ ያለ ነው" ብለዋል።
"ቀበሌው ላይ የነበረው ንብረት ሙሉ ለሙሉ የወደመበት ጥቃት ነው የተፈጸመው። የተፈጸው ድርጊት ያማል። አንድ ቀበሌ ወድሟል። ቤት፣ ንብረት የሚባል ነገር የለም። ያስከተሏቸው መሳሪያ ያልያዙ ግለሰቦች ነዳጅና ቤንዚን ይዘው ነው ታጣቂዎቹ ጥቃት ከከፈቱ በኋላ ሙሉ በሙሉ ቀበሌውን ያቃጠሉት" ብለዋል።
"ጥቃት ለመፈጸም እንደ መንደርደሪያ የሚጠቀሙት 8ኛ፣ 4ኛ ከሚባሉ አካባቢዎች ነው። ይህ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት የተለያዩ ምልክቶች ይታዩ ነበር፤ ታጣቂዎቹ ጥቃት ለመፈጸም ሲሰባሰቡ ለሚመለከታቸው መረጃ ብንሰጥም የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ቦታው ላይ ገብተው እርምጃ ያለመውሰድ ችግር ነበር" ነው ያሉት።
የክልሉ ምክር ቤት አባል አቶ ለሜሳ ኔኖ ትናንት የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዱ፣ መከላከያ በቦታው ገብቶ በጥቃቱ ከአካባቢው የሸሹ ሰዎችን እያሰባሰበ መሆኑም ሲገልጹ፣ ነዋሪዎችም በስፍራው የሚስተዋለው ጥቃት በዘላቂነት እንዲያስቆም ጠይቀዋል።
ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ?
የካማሺ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አካል አቶ ቦካ አቦሴ፣ በቀበሌው ጥቃት ተፈጸመ መባሉን "ትክክል ነው። ጸረ ሰላም ኃይሎች ጥቃት አድርሰዋል። ቤት ንብረት ወድሟል" ብለዋል። ቦታው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።
በጥቃቱ የደረሰውን የጉዳት መጠን የሚመለከት ዝርዝር መረጃ ገና እንዳልደረሳቸው፣ ሲደርሳቸው እንሚያሳውቁ ገልጸው፣ አሁን አካባቢው በሰላማዊ ሁኔታ እንደማገኝ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia