ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#Amhara

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#Amhara
#Amhara

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ከሰኔ 3-5/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና 173,699 ተማሪዎች ውስደው ነበር።

ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ተማሪዎችም ውጤታቸውን https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ ፤ በሚመጣው ቅጽ ላይ የተማሪ መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት ፤ ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ።

ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው https://amhara.ministry.et/#/complaint ላይ በመግባት ቅሬታቸው ማቅረብ እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች