ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#Merkato ባለፈው ዓመት 2017 ዓ/ም የእሳት አደጋ ባጋጠመበት የአፍሪካ ትልቁ ገበያ መርካቶ ዛሬ ከምሽት 1 ሰዓት ገደማ አንስቶ ለሰዓታት በቆየ የእሳት አደጋ ንብረት ላይ ውድመት ደር…

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#Merkato ባለፈው ዓመት 2017 ዓ/ም የእሳት አደጋ ባጋጠመበት የአፍሪካ ትልቁ ገበያ መርካቶ ዛሬ ከምሽት 1 ሰዓት ገደማ አንስቶ ለሰዓታት በቆየ የእሳት አደጋ ንብረት ላይ ውድመት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው " ጣሳ ተራ " ፣ የጨርቃ ጨርቅ አልባሳት መሸጫ መጋዘኖች ላይ ነው።

ለሰዓታት በዘለቀው የእሳት አደጋ በስፍራው የሚሰሩ ነጋዴዎች ንብረታቸውን ለማሸሽ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርጉ ነበር።

እሳቱ ከሰዓታት በኋላ ቢጠፋም ስለ አደጋው ዝርዝር መረጃ እና መነሻ ምክንያት በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።

ባለፈው ዓመት በዚሁ በመርካቶ ትልቃ የገበያ ስፍራ " ሸማ ተራ " አካባቢ ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ ከባድ የእሳት አደጋ ደርሶ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች