ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#NationalDialogue🇪🇹

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#NationalDialogue🇪🇹
#NationalDialogue🇪🇹

በ10 እና 50 ሰዎች የተደራጁ ጥቃቅንና ንዑሳን ቡድኖች ያቀረቧቸው የምክክር ሀሳቦች በ250 ሰዎች ለተደራጀው “ስልታዊ” ቡድን እንዲቀርቡ ተደርጎ ከተገመገሙ በኋላ ወደ 500 ሰዎች የተደራጀው ትልቁ ቡድን ምክክር እንደሚተላለፍ ቢጠበቅም ሂደቱ እስካሁን አለመጀመሩ ተገለጸ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተሳታፊዎችና ከምክክር ኮሚሽኑ ባገኘው መረጃ የንዑሳን ቡድኖች ያቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦች እየተጠናቀቁና እየተገመገሙ መሆኑን ተረድቷል።

ተሳታፊዎች እንደገለጹት በሂደቱ የተያዙ አንዳንድ ሀሳቦች በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመጠቆም ተጨማሪ ግምገማና ማስተካከያ እየተደረገባቸው ነው።

ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር) ፥ ቀደም ሲል የ500 ሰዎች ቡድን ምክክር ሰኞ እንደሚጀመር ቢገለጹም ፥ አሁን ግን ሂደቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ገልጸዋል።

መስፍን (ፕ/ር) እንዳሉት፣ አንዳንድ ቡድኖች ሀሳቦቻቸውን በፍጥነት ሲያጠናቅቁ ሌሎች ደግሞ ሀሳቦችን በድጋሚ በማዳመጥ፣ በማስተካከልና በማዳበር ላይ ናቸው።

16ቱ የስልታዊ ቡድን ክፍሎች ሂደታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የተለያዩ አጀንዳዎች ወደሚመከሩበት የ500 ሰዎች ጉባዔ እንደሚተላለፉ ተገልጿል።

ኮሚሽነሩ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ የ500 ሰዎች ጉባዔ በቀጣዩ ቀን ሊጀመር እንደሚችል ነገር ግን ያልተጠናቀቁ አጀንዳዎች ካሉ ወደ ቀጣይ ቀናት ሊዘዋወር እንደሚችል ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች