#SaudiArabia
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#SaudiArabia
በሳዑዲ አረቢያ በቀጥታ የማኅበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ስርጭት ላይ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል የተባለ ኢትዮጵያዊ ከአምስት ግብረ አበሮቹ ጋር በሳዑዲ የጸጥታ አካላት መያዛቸውን በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
ኤምባሲው እንዳለው፣ በሳዑዲ ድንበርና በረሃማ አካባቢዎች በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን መካከል ግጭትና ግድያ መፈጸሙን ተከትሎ ጉዳዩ በቅርበት ሲከታተል ቆይቷል።
በተጨማሪም ጉዳዩን በማኅበራዊ ሚዲያ በማሰራጨትና በማራገብ ተጠርጥረው ከ100 በላይ ግለሰቦች መያዛቸውንና ጉዳያቸውም በሕግ እየታየ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia