ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#ሳይንስ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#ሳይንስ
#ሳይንስ

በአሜሪካ የዘረመል ማሻሻያ ከተደረገለት አሳማ የተወሰደ ኩላሊት በሰው ሰውነት ውስጥ 271 ቀናት በመሥራት እስካሁን ከተመዘገቡት ረጅሙ ጊዜ ሆኗል።

66 ዓመቱ ቲም አንድሪውስ በደረሰበት የኩላሊት ሕመም ምክንያት ዲያሊሲስ ይደረግለት ነበር። ከአሳማ የተወሰደው ኩላሊት በ2017 ጥር ወር ተተክሎለት ወዲያውኑ መሥራት ጀምሯል።

ኩላሊቱ ለ271 ቀናት ከሠራ በኋላ ተወግዶ፣ አንድሪውስ ለ82 ቀናት ወደ ዲያሊሲስ ተመልሷል። በኋላም ከሰው ለጋሽ የተገኘ ኩላሊት ተተክሎለት አሁን በጥሩ ሁኔታ እየሠራ ነው።

ይህ ሂደት ዜኖትራንስፕላንቴሽን ይባላል፤ ማለትም ከሌላ የእንስሳት ዝርያ የተወሰደ አካልን በሰው ላይ መትከል ነው። አሳማዎች የአካላቸው መጠን ከሰው ጋር በመመሳሰሉ ለዚህ ምርምር ተስማሚ እንስሳት ናቸው።

ችግሩ የሰውነት መከላከያ ሥርዓት የአሳማውን ኩላሊት እንደ "እንግዳ አካል" በመቁጠር ሊያጠቃው መቻሉ ነው። ስለዚህ ሳይንቲስቶች 69 የዘረመል ማሻሻያዎች የተደረጉባቸውን አሳማዎች በማዘጋጀት ኩላሊታቸው ከሰው አካል ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ሞክረዋል።

የምርምሩ ትልቁ ተስፋ፣ የሰው ኩላሊት ለጋሾች እስኪገኙ ድረስ የአሳማ ኩላሊቶችን እንደ ጊዜያዊ መፍትሔ መጠቀም መቻል ነው።

በአሜሪካ ብቻ ወደ 100 ሺህ ሰዎች የኩላሊት ለጋሽ በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ፣ በዓመት የሚከናወኑት ንቅለ ተከላዎች ወደ 25 ሺህ ብቻ ናቸው። ይህም እንደዚህ ያሉ የአሳማ አካላት ምርምሮች ለምን እየተሰፋፉ እንደሆነ ያሳያል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች