የጃፓናውያን እድሜ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የጃፓናውያን እድሜ
በጃፓን 100 ዓመት የደፈኑ እና ከዛ በላይ የሆናቸው ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ አለፈ።
በጃፓን ዕድሜያቸው 100 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ሺህ አልፎ 107,677 መድረሱን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከእነዚህ ውስጥ 88 በመቶው ሴቶች ሲሆኑ በኪዮቶ ከተማ የሚኖሩት የ114 ዓመቷ ኪሺሞቶ ፉዮ በእድሜ እጅግ የገፉት ሴት ናቸው።
የጃፓን ጤና ሚኒስትር ኬኒቺሮ ኡኖ፤ የህክምናና የቴክኖሎጂ እድገት ሰዎች ረጅም እድሜ እንዲኖሩ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል።
ባለሙያዎች የጃፓናውያንን ረጅም ዕድሜ ከጤናማ አመጋገብና ንቁ ከሆነ የአኗኗር ዘይቤ ጋር ያያይዙታል።
የጃፓን ምግብ በአብዛኛው ፦
- በዓሣ
- በአትክልት
- በሩዝ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከሌሎች ብዙ ሀገራት አንጻር የስብ መጠናቸው የቀነሰ ነው።
በጃፓን በአዛውንቶች ዘንድ በእግር መሄድ፣ ብስክሌት መጠቀምና አካልን ማንቀሳቀስ የተለመደ ነው።
እ.ኤ.አ. በ1963 በጃፓን የ100 ዓመትና በላይ ሰዎች ቆጠራ ሲጀመር 153 ብቻ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን ቁጥሩ 107,677 ደርሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የጃፓን ህዝብ እድሜ እየገፋ የልደት መጠን እየቀነሰ መሆኑ አሳሳቢ መሆኑ አልቀረም።
የ65 ዓመትና በላይ የሆኑ ሰዎች አሁን ከሀገሪቱ ህዝብ 30 በመቶ ያህሉን ይይዛሉ፤ ይህም በ2070 ወደ 40 በመቶ ሊጠጋ ይችላል።
በተመሳሳይ የልደት መጠን እየቀነሰ ሲሆን ባለፈው ዓመት የጃፓናውያን የልጆች መውለድ መጠን 1.14 በመሆን አዲስ ዝቅተኛ ሪከርድ ተመዝግቧል።
በ2070 የሀገሪቱ ህዝብ ወደ 87 ሚሊዮን ሊቀንስ እንደሚችል ተገምቷል።
ስለዚህ ጃፓን በአንድ በኩል ረጅም ዕድሜ የሚኖሩ ዜጎቿ ቁጥር በመጨመሩ ስትደሰት፣ በሌላ በኩል የህዝብ እርጅናና የልደት መጠን መቀነስ የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓቷን ለማስቀጠል ፈተና ሆኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia